የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍ 4 ሺሕ 210 መጻሕፍትን አበረከተ

ግንቦት 19/2014(ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍ 4 ሺሕ 210 መጻሕፍትን አበረከተ።

መጻሕፍቱን ያስረከቡት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምጸሐይ ጳውሎስ የተበረከቱ መጻሕፍት የታሪክና የተለያዩ ይዘት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጽሕፈት ቤታቸው በእውቀት የተገነባ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ የድርሻቸውን ለመወጣት መጻሕፍቱን መለገሳቸውንም ተናግረዋል።

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሀና (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት ቤተ መጻሕፍትን በመጽሐፉ መሙላት አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የበለፀጉት አገራት የእድገታቸው ምክንያት እውቀት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ እንደ ሀገር ብልጽግናን ለማረጋገጥ በተለያዩ መስኮች እውቀት ያለው ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

እውቀት አንድም ከመደበኛ ትምህርት በሌላ በኩል ከቤተ መጻሕፍት መጽሐፍ በማንበብ እንደሚገኝና “ሚሊዮን መጻሕፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ” በሚል የተጀመረው የመጻሕፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ሳይጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመስከረም ቸርነት