1ሺሕ 166 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

ግንቦት 19/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 166 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 169 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 133ቱ ደግሞ ህጻናትና መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተመላክቷል።

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ29 ሺሕ 120 በላይ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡