በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ተካሄደ

የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) ከፌዴራል እና ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮዎች የተውጣጡ አመራሮችና ሰራተኞች በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ።

የክረምት ወቅት እንደመሆኑ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመርኃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ተናግረዋል።

በተለይም ድሬዳዋ ሞቃታማ አካባቢ እንደመሆኗ መጠን የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር መካሄዱ ፋይዳው የጎላ ነው ተብሏል።

እንደ ችግኙ ሁሉ ኢንዱስትሪውንም ከስር መሰረቱ በመንከባከብ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተጠቁሟል።

ሱራፌል መንግሥቴ (ከድሬዳዋ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW