አትሌት ጎይትቶም ገብረስላሴ ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘች

አትሌት ጎይትቶም ገብረስላሴ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) አትሌት ጎይትቶም ገብረስላሴ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘች፡፡

በአራተኛ ቀን 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውሎው የሴቶች ማራቶን ውድድርን ያስተናገደ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጎይትቶም ገብረስላሴ 1ኛ በመውጣት ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።

ጎይትቶም ገ/ስላሴ አንደኛ ከመውጣቷም ባሻገር በሴቶች ማራቶን የዓለም ሻምፒዮን ሺፕ ሪከርድ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ18 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት መስበር ችላለች።

እስከ ውድድሩ መጠናቀቂያ ቦታ ድረስ ኬንያዊቷን አትሌት በመከተል እና በማስጨነቅ በድንቅ የአሯሯጥ ብቃት ስትከተል የቆየችው አትሌቷ የመጨረሻውን 400 ሜትር ፍጥነት በመጨመር ተነጥላ በመውጣት አሸንፋ ወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ማስገኘት ችላለች፡፡

ፔፕቱም ኮሪር ውድድሩን በሁለተኝነት ስታጠናቅቅ፤ አትሌት አባብል የሻነህ ባጋጠማት ህመም ሩጫውን መጨረስ አልቻለችም።

የውድድሩን የነሐስ ሜዳሊያ ትውልደ ኬንያዊቷ ለእስራኤል የሮጠችው ሳልፒተር ወስዳለች።

ኢትዮጵያ እስካሁን ካደረገችው አራት የፍፃሜ ውድድሮች በሦስቱ ወርቅ በማግኘት በድምሩ አራት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ !!

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!