ሐምሌ 27/2014(ዋልታ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 3 ቢሊየን 405 ሚሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የክልሉን መንግሥት የ2015 በጀት አፅድቋል።
የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልባሲጥ አቡበከር ከተያዘው በጀት 51 በመቶ ለካፒታል በጀት እንዲሁም 49 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ በጀት የሚውል መሆኑን ገልጸዋል።
በጀቱም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች ከሚሰበሰብ ገቢ እና ፌዴራል መንግሥት ድጎማ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ ከበጀቱ በተጨማሪ፣ የሀረር ከተማ መዋቅራዊ ፕላን፣ የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ በአዲስ ለማዋቀር የወጣውን አዋጅ፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ እና የምክር ቤት አባላት የሥነ ምግባር ደንብ አዋጅንም መርምሮ አፅድቋል።
በተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)