የተገኙ የማክሮ ኢኮኖሚ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሐምሌ 27/2014(ዋልታ) የተገኙ የማክሮ ኢኮኖሚ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባ ማካሄዳቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር መታየቱንም ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደሆነም አረጋግጠናል ብለዋል።