በክልሉ የዝናብ እጥረት ያለባችዉን አካባቢዎች ለማልማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

መስከረም 14/2015 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የዝናብ እጥረት ያለባችዉን አካባቢዎች ለማልማት ምርጥ ዘር በማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው ምክትል ኃላፊ ጌቱ ገመቹ የሚመራ ልዑክ በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ቶኩማ ቀበሌ በክላስተር የለማ የስንዴ እና ማሽላ ማሳ ጎብኝቷል።

በወረዳዉ ከዚህ በፊት ማሽላ ሲዘራ መቆየቱን የገለፁት የዞኑ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ሁሴን ሙሀመድሁሴን በክልሉ የግብርና ባለሞያዎች እንዲሁም በተለያዩ አካላት ሲደረግ በነበረው ድጋፍ ስንዴ ማምረት መቻሉን አመላክተዋል።

የቢሮ ምክትል ኃላፊ በበኩላችዉ በክልሉ በክረምት እርሻ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በምርት መሸፈኑን ከዚህ ዉስጥም ከ4 ሚሊየን በላዩ በክላስተር መሸፈኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የዝናብ እጥረት ያለባችዉን አካባቢዎች ለማልማት ምርጥ ዘር በማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በዘጠኝ ወር የሚደረስ ማሽላ እየተዘራ እንደነበር የገለፁት የቶኩማ ቀበሌ አርሶአደሮች በዘንድሮው አመት 2 ሺሕ 100 ሄክታር መሬትን በክላስተር በመደራጀት የስንዴ ምርት ማምረታችዉን ተናግረዋል።

በዚህም ባለሞያዎች የተለያዩ ድጋፍ ሲያረጉላችዉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ፌናን ንጉሴ (ከምዕራብ ሀረርጌ)