ብሔራዊ ቡድኑ ለመልስ ጨዋታ ኮንጎ ገባ

መስከረም 15/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለመልሱ ጨዋታ ወደ ኮንጎ አምርቷል፡፡

ቡድኑ ባሳለፍነው ሐሙስ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ጨዋታውን አከናውኖ ያለ ጎል አቻ መለያየቱ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኮንጎ ጉዞ በፊት በትናንትናው ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል።

ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንሳሻ ያመራ ሲሆን ጨዋታውንም ማክሰኞ እንደሚያከናውን ከኢትዮጵያ እግር ኳን ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡