ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ኅዳር 5/2015 (ዋልታ) ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ደረጃ 1 ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር እና ፍኖተ ፅድቅ የበጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን ነው ተብሏል፡፡

የተደረገው ደጋፍ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዊልቸር እና የተለየዩ የህክምና መድኃኒት መሆኑም ተገልጿል፡፡

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ም/አዛዥ ለሰ/ሃ/ልማት ሜ/ጄኔራል አብድሮ ከድር ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ሰራዊታችን በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ በህዝባችን ድጋፍ ታግዞ አመርቂ ድል እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሀገራችን ሰላም ለማስጠበቅ እና በዘላቂነት ኢትዮጵያን ለማሻገር ሁላችንም ሀገራዊ ኃላፊነት አለብን ያሉት ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ለወደፊትም አብሮነታችሁ አይለየን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የኢትዮጲያ ዲያስፖራ ማህበር ተወካይ ሻምበል ተፈሪ እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ ሰራዊቱ ከሚከፍለው ውድ ህይወት የሚበልጥ ስላልሆነ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በተለያዩ ጊዜ ድጋፍ ላደረጉ የዲያስፖራ አባላት የእውቅና ሰርተ-ፊኬት እንደተበረከተላቸው ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW