“አሻራ” የተሰኘ መጽሐፍ በአፋርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለአንባቢያን ቀረበ

ታኅሣሥ 26/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ያደረጓቸውን ንግግሮች የያዘው “አሻራ” የተሰኘ መጽሐፍ በአፋርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለአንባቢያን ቀረበ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጓቸው ንግግሮች በመጽሐፍ መልክ “አሻራ” በሚል ስያሜ መዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ በእስካሁኑ ጉዞዋ በተዛቡ ትርክቶች በርካታ ችግሮች እየገጠሟት ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲያግዝ ብሎም ለወደፊት ታሪክን ለመዘገብ ሲባል መጽሐፉ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

በመጽሐፉ ምረቃ ስነ ስርዓት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዙፋን አምባቸው (ከሰመራ)