ራስ መንገሻ ስዩም ታሪካዊ ሰነዶችን ለውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር አበረከቱ

የካቲት 27/2015 (ዋልታ) በ1960ዎቹ የህዝብ ስራዎች እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር የነበሩት ራስ መንገሻ ስዩም ለውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር ታሪካዊ ሰነዶችን አስረከቡ፡፡

ሰነዶቹን ከራስ መንገሻ የተረከቡት የውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) “ከክቡርነታቸው ብዙ ነገሮችን ለማወቅ እና ለዲጅታል አውደ-ርዕይ ማዕከል ጠቀሜታ ያላቸው ተጨማሪ ሰነዶችን እንጠብቃለን” ሲሉ በትዊትር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ራስ መንገሻ ስዩም የህዝብ ስራዎች እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የአሁኑ ውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር፤ የውሃ ልማት ዳይሬክቶሬት በሚል ስያሜ እሳቸው በሚመሩት ተቋም ስር እንደነበረም በመረጃቸው አስታውሰዋል፡፡