የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ውይይት ተካሄደ

የካቲት 27/2015 (ዋልታ) የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከደቡብ ኮሪያ የዓለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት ዋና ጸሃፊ ሁን ሞክ ሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይም በጫማ ስራ ላይ የተሰማሩ የኮሪያ ባለሃብቶችን በኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩም  ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ዘርፉን ሊያነቃቁ የሚችሉ “የማይንድ ሴት” ስልጠናን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡