የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

መጋቢት 26/2015 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጫላ ዋታ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብታቸውን አነሳ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤውም የፍትሕ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የምክር ቤት አባልና የቀድሞው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጫላ ዋታ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል፡፡

ጫላ ዋታ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የመንግስት ግዢ ስርዓትን ሳይከተሉ የተለያዩ ግዢዎችን ፈጽመዋል በሚል በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡