በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህትማማቾች 7 ሺሕ መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለገሱ

መጋቢት 29/2015 (ዋልታ) በአሜሪካ የሚኖሩ ሁለት እህትማማቾች በትውልድ ኢትዮጵየውያን ወጣቶች ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ያሰባሰቡትን 7 ሺሕ መፃሕፍትን ለኢትዮጵያ ኤምባሲ አስረረከቡ።

በልጆቻቸው በኩል የተሰበሰቡትን መፃሕፍት ለኤምባሲው ያስረከቡት እናታቸው አያንቱ አበበ ልጆቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዲኖራቸው ለማድረግና የበጎ ስራ አርዓያ እንዲሆኑ ይህ መፃሕፍትን የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን አውስተዋል።

የተለገሱት መጻህፍት በኢትዮጵያ የንባብ ባህል እንዲዳብር፣ ቤተ መጻሕፍት የተሟላ አቅርቦት እንዲኖራቸው ለማገዝ ነውም ተብሏል።

የተለገሱት መጻሕፍት ቋንቋ፣ ሥነ ህይወት፣ የታሪክ፣ የሂሳብ፣ የምርመርና ሌሎች ጠቃሚ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ እንደሆኑ ሁለቱ እህታማቾች  ገልጸዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ይህን መሰል ትውልድን የሚያንጹ መፃሕፍት በመለገስ ለተደረገው አርዓያነት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

መፃሕፍቶቹም ከሌሎች መሰል የዳያስፖራ ወገኖች ከተለገሷቸው ጋር በመሆን ለአብርሆት ቤተ-መፃሕፍት የሚላኩ መሆናቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል።