የቀድሞው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብረካን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው


ነሐሴ 5/2015 (አዲስ ዋልታ) ላለፉት አራት ዓመታት ስራ አቁሞ የነበረው አይካ አዲስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ቡሉኮ ኢንቲግሬትድ ቴክስታይል በሚል ስም ዳግም ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፋብሪካውን የጎበኙ ሲሆን ወደ ስራ መመለስ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

የከፍተኛ አመራሮች የመስክ ጉብኝት ፋብሪካው ከሚፈጥረው በርካታ የስራ ዕድል በተጨማሪ ለሀገር የሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ዳግም ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፋብሪካውን የኦሮሚያ የልማት ድርጅት ከግል ባለሀብቶች ጋር በመሆን ወደ ስራ ለማስባት እየተሰራ ሲሆን ሚኒስቴሩም በጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የተዘጉና ስራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንንዲገቡ የሚያደረገውን የድጋፍና ክትትል ማዕቀፍ መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ድርጅቱ በስሩ ከ7 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ ዕድል የፈጠረ እና ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የነበረው ፋብሪካ መሆኑ ይታወቃል፡፡