የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

 

ነሐሴ 5/2015 (ዋልታ) የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰት ብሩታ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አደርገውላቸዋል ።

 

አምባሳደር ብርቱካን የሁለቱ አገራት ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

 

የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።