ከንቲባ አዳነች አቤቤ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላትን ጎበኙ

ነሐሴ 7/2015 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል አካባቢ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት አካባቢ ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

እነዚህ በመገንባት ላይ የሚገኙት የግብርና ምርት የገበያ ማዕከላት፣ ምርትን በስፋት ወደ ከተማዋ ማስገባት የሚስያስችል መሆኑና በከተማዋ ያለውን ህገወጥ የገበያ ትስስር ሰንሰለት የሚያስቀር እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉና ለነዋሪዎች ተጨማሪ የስራ እድል የሚፈጥሩ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የጀመርናቸው ፕሮጀክቶቻችንን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት በማጠናቀቅ በቅርብ ቀን ለአገልግሎት ክፍት እናደርጋለን ብለዋል።

ከንቲባዋ አክለውም የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ላሳየዉ የግንባታ ብቃት ምስጋና አቅርበዋል፡፡