የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት መተኮስ ክልክል ነው – የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ

ነሐሴ 12/2015 (አዲስ ዋልታ) የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህንኑ የፀጥታ ስራ በአግባቡ ለመምራት እና ለመቆጣጠር ሲባል እንዲሁም አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በቡሄ በዓል የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓት ወቅት ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡