ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ነሐሴ 12/2015 (አዲስ ዋልታ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ” መሆኑን አመልክተዋል።

ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አክለዋል።