የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ነሐሴ 15/2015 (አዲስ ዋልታ) የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ መጀመሩን ገልጸው የሁለተኛውን የመካከለኛ (2016-2018) ዕቅድንም እንገመግማለን ብለዋል።

በመድረኩ የ2016 ዋና ዋና አቅጣጫዎች እንደሚታዩም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የ100 ቀን የመጨረሻውን ሩብ ዓመት የእያንዳንዱን ተቋም አፈጻጸም እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡

 

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የሚሰሩ ሥራዎች ምን ዓይነት ቅርጽ እና መልክ አላቸው የሚለውን ለመመልከት መድረኩ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡