በኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢንዱስትሪን ለመፍጠር በምርምርና ጥናት መታገዝ እንደሚገባ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ

ነሐሴ 17/2015 (አዲስ ዋልታ) በኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢንዱስትሪን ለመፍጠር በምርምርና ጥናት የታገዙ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገለጹ።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ያሉበትን ክፍተቶች የሚለይበትና ያለውን አቅም ማጠናከር ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደጥናት እየተከሃደ ነው፡፡

ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የተሻለ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር ከአርባ ዓመታት በላይ በርካታ የማማከር ስራዎችን የሰራ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከ600 በላይ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆነውን ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎትን በማጠናከር ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በማማከርና በስልጠና ኢንዱስትሪዎችን የሚያግዝ ግዙፍ አፍሪካዊ ተቋም መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑም በአውደ ጥናቱ ላይ ተነስቷል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ምሁራን ተገኝተዋል።

በዙፋን አምባቸው