አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከካናዳ የኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ


መስከረም 5/2016 (አዲስ ዋልታ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከካናዳው የኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ምክትል ሚኒስትር ስካት ሃሪስ ጋር የሁለቱን አገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ውይይት በግዚያዊ የስራ ቅጥር በከፍተኛ የትምህርት ዕድልና በቪዛ አሰራሮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በካናዳ ህግ መሰረት በግዚዊነት ሊሰሩ የሚችሉበትን እድሎች እውቀትና ክህሎታቸውን ለማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያታቸውም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን በካናዳ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው መማር የሚችሉባቸውንና የሁለቱ ሀገራትን የባህል ልውውጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉደዮችም ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የቪዛ አሰራር በማቅለል ንግድ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን በማጎልበት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማሳደግ በሚያግዙ ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል፡፡