የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ

መስከረም 7/2016 (አዲስ ዋልታ) የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባባሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡

በዛሬው ዕለት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተካሄደው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በመቀጠል በዩኔስኮ የተመዘገበ የኢትዮጵያ ሁለተኛው የተፈጥሮ ቅርስ እንደሆነም ተጠቁሟል።

45ኛው የዓለም የቅርስ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻዎችን በዓለም ቅርስነት ማስመዝገቧም ተመላክቷል፡፡