የዓለም አቀፍ ቴሌኮም ሕብረት አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

መስከረም 22/2016 (አዲስ ዋልታ) የዓለም አቀፍ ቴሌኮም ሕብረት አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን “ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለዘላቂና ፍትሐዊ መጻኢ ጊዜ፤ የአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ይህ ፎረም ትልቅ ሚና አለው።

በመድረኩ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ፣ ከአፍሪካ የሕብረቱ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ተቋማት እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይቆያልም ነው የተባለው፡፡

በብሩክታዊት አፈሩ