አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከፓኪስታኑ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ምባሳደር ምስጋኑ አረጋና በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሚአን አቲፍ ሻሪፍ

ጥቅምት 28/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሚአን አቲፍ ሻሪፍ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያዩ፡፡

የሁለቱ ውይይት በዋናት ያተኮረው የኢትዮ-ፓኪስታን ታሪካዊ ግንጉኙትን ማጠናከር በሚቻለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ ሁለቱ አገራ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአቪዬሽን፣ በባህልና ቴክኒካል ትብብር ዙሪያ ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመው ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ሁኔታዎች የተመቻቹ መሆናቸውና የፓኪስታን ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ማኢን አቲፍ በበኩላቸው አገራቱ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት መኖሩን ጠቁመው መንግስታቸው በሁለትዮሽም ሆነ በባለ ብዙ ወገን መድረክ የበለጠ እንዲጠናከር ፍላጎት እንዳለው መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደሩ አክለውም ኢትዮጵያ በእርሻ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በፋርማሲዩቲካል እና በግንባታው ዘርፍ ግዙፍ የኢንቨስትመንት አቅም እንዳት ጠቁመው ለፓኪስታን ባለሃብቶች ጥሩ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡