ኢ/ር ታከለ በተጓተቱ የውሃ ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ ጉዳዮች ዙሪያ ከብሄራዊ ባንክ ገዥ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዲናዋ በውጭ ምንዛሬ እጥረት በተጓተቱ የውሃ ፕሮጀክቶች ማስፋፊያና ጥገና ስራዎች ዙሪያ ከብሄራዊ ባንክ ገዥው ዶክተር ይናገር ደሴ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በከተማዋ ያለውን ከፍተኛ የውሃ ፍላጎት ለማሻሻል የከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸው የለገዳዲ 16 የከርሰ ምድር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና የለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ጉዳዮች መነሳታቸውም ተገልጿል።

አሁን ላይ ለአዲስ አበባ ከተማ በቀን የሚቀርበውን የውሃ መጠን እና ተደራሽነት ለማሳደግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት መጓተታቸው ተጠቁሟል።

በዚህም ለለገዳዴ የውሃ ጉድጓዶች እና የውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክት ማስፋፊያ፣ ለቦሌ አራብሳ ቤቶች ፕሮጀክት የፍሳሽ ማጣሪያ ስራዎች እንዲሁም፥ የድሬ የውሃ ግድብ ጥገና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት  አስታውቋል ።(ኤፍ.ቢ.ሲ)