ቻይና የመጀመሪያ የአንታርቲካ አየር ማረፊያ ልትገነባ ነው

ቻይና የመጀመሪያ የአንታርቲካ አየር ማረፊያ ልትገነባ እንደሆነ አስታወቀች፡፡

በአለም የተለያዩ ሃገራት ዘመናዊ አየር ማረፊያዎችን ገንብተዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ አንዷ ደግሞ ቻይና ነች፡፡

አንታርቲካ ደግሞ የአለማችን በረዶአማዉ ክፍለአለም ቢሆንም የተለያዩ ሃገራት አየር ማረፊያቸዉን በአንታርቲካ የገነቡ ሲሆን በአየር መንገድ ግንባታዉ በቅርቡ በግዝፈቱ የመጀመሪያ የሆነዉን አየር መንገድ የገነባችዉ ሃገር ቻይና አንታርቲካ ዉስጥ ግን የራሷ የሆነ አየር መንገድ ሳትገነባ ቆይታለች፡፡

ታዲያ አሁን ከወደ ቻይና የተሰማዉ ዜና ግን ሃገሪቱ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ህዳር ወር አየርመንገድ ልትገነባ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ቻይናዊያን አስከአሁን ወደ ደቡቡ የአለም ክፍል መብረር ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን ለዚህ ደግሞ የሃገሪቱ የመጀመሪያ ፖላር የአዉሮፕላን ማረፊያ ዡይንግ 601 ከመነሻ ጋር የሚገናኝበት መስመር የዛሬ ሶስት አመት ከአገልግሎት ዉጪ ሆኖ በመቆየቱ ነዉ፡፡

ከዚህ ቀደም ሲል ቻይናዊያን ተመራማሪዎች ዙሎንግ የተሰኘች መርከብን በመያዝ በበረዶ ወደ ተሸፈነዉ አንታርቲካ በመጓዝ ጥናት አድርገዋል፡፡ በዚህም ያለዉ ርቀት በአዉሮፕላን ከሚፈጀዉ ይልቅ በመርከብ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያረጋገጡ ሲሆን ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የአየር በረራ አገልግሎት መክፈት ተመራጭ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

አሁን ባለዉ መረጃ አንታርቲካ ዉስጥ ከ 20 የሚበልጡ ሃገራት አየር መንገዶች ያሉ ሲሆን ቻይናም ዢዉይንግ 601 አየር መንገድ  በሩስያ አየር መንገድ ላይ ተደርቦ  አዉሮፕላኖች  መነሻና ማረፊያ የሚያገለግል ሲሆን ይህ ደግሞ ለመቆጣጠር አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ለዚህም ነዉ ቻይና የራሷን አየርመንገድ ለመገንባት ያቀደችው፡፡ ታዲያ ሃገሪቱ የምትገነባዉ አየር መንገድ በርካታ ተግዳሮቶች እንደሚኖሩትም ከወዲሁ አስቀምጣለች፡፡ ይህ ደግሞ አንታርቲካ ላይ የሚገነባዉ አየር መንገድ ሌላ ቦታ እንደሚገነባዉ ቀላል እንደማይሆንና በተለይም ደግሞ አህጉሩ በበረዶ የተሸፈነ በመሆኑ ከምንም በላይ አስቸጋሪ እንደሚሆን ነዉ የተገለጸው፡፡

በተለይም በየጊዜዉ እየቀለጠ የመጣዉ የበረዶዉ ግግር ከምንም በላይ ግንባታዉን አስቸጋሪ የሚያደርገዉ ሲሆን አደጋዉን ለመቀነስ ግንባታዉ የበረዶ ግግሩ ከሚቀልጥበት ስፋራ ራቅ በማለት በዝግታ ወደሚቀልጥበት ቦታ ለመገንባት ታስቧል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሌላዉ ተግዳሮት ደግሞ እንደ ጥጥ የሚበተነዉ በረዶ ነዉ፡፡ በአካባቢዉ ባለዉ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ምክንያት የሚኖረዉ በረዶ አዉሮፕላን የሚነሳበትና የሚነሳበትን መንገድ በመሸፈን ፈታኝ የሚያደርገዉ ቢሆንም መንገድ ጠራጊ የሚሽከረከር ማሽን ለመጠቀም ታቅዷል ሲል ሲጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡