41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።

በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት 41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ግለሰቦቹ በቶጎ ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መያዛቸውን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ተናግረዋል።

መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልም መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ በተጠናከረ መልኩ እየሠራ የሚገኝ መሆኑን አቶ ደመላሽ ተናግረዋል።

ህዝቡ እያደረገ ስላለው ንቁ ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡት ሥራ አስኪያጁ፥በቀጣይ ህገ ወጦችን በንቃት በመከታተልና ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።  (ምንጭ: የኢትዮጵያ ገቢዎችና እና ጉምሩክ ባለስልጣን)