ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሱዳን ገቡ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሱዳን  መግባታቸው ተገለጸ።  

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ቆይታቸው ከሱዳን  ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ዘላቂ ትብብር የውይይታቸው የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ።(ምንጭ: የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት )