ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውንና የፖለቲካ ተሳትፏቸውን ማሳደግ ይገባቸዋል-  ጠቅላይ  ሚንስትር  ኃይለማርያም  

በአገሪቱ  የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች   በተደራጀ  ሁኔታ  በመንቀሳቀስ  ኢኮኖሚያዊ  ተጠቃሚነታቸውን  ማረጋገጥና ፖለቲካዊ  ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ  ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው  የ4ኛው  አገር  አቀፍ  የወጣቶች የንቅናቄና ተሳትፎ ኮንፈረንስ ገለጹ ።
በኮንፈረንሱ ከ3ሺበላይ የሚሆኑ ከዘጠኝ ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች  የተውጣጡ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን  ወጣቶቹ  በተወካዮቻቸው  አማካኝነት በመልካም አስተዳደር ፣ በሥራ አጥነት ፣ በሰላም ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ፣ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደት ፣ በወጣት አደረጃጀቶችና በተለያዩ ጉዳዮች  ላይ ለቀርቡላቸው ጥያቄዎች  ምላሻቸውን ሠጥተዋል ።
እንደ ጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማርያም ገለጻ የአገሪቱ ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና   ፓለቲካዊ  ተሳትፎ  ለማሳደግ  የወጣቶች  ፓኬጅ   ቀደሞ  እንዲዘጋጅ   ተደርጓል ብለዋል ።
በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች የሚያገጥሟቸውን ችግሮች መፍታት ወሳኝነት ያለው ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቱ ደረጃ በደረጃ የሚታዩ  ክፍተቶችን ለመሙላት  መንግሥት  በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸዋል ። 
የአገሪቱ ወጣቶች በበኩላቸው ድህነትን  ለማሸነፍ በሚያስችል መልኩ በመነሳሳት ከመንግሥት በተጨማሪ አዳዲስ ሥራዎችን በመፍጠር በኩል የራሳቸውን ድርሻ  መወጣት  እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።
ዘመናዊ የግብርና ሥራ ለአገሪቱ  ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ዘርፍ  ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ  ወጣቱ ከመንግሥት ከመንግሥት  ባሻገር ወጣቱ በቁርጠኝነት   በመነሳት  የዘርፉን  እምቅ  ኃይል አሟጦ ሊጠቀምበት እንደሚገባ አስረድተዋል ።  
ሌላው  ለአገሪቱ  ወጣቶች  ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያስችል  የተናገሩት በመላ አገሪቱ እየተካሄደ  ያለው  የመሠረተ ልማት  ግንባታ ሥራ ሲሆን በገጠር መንገድ ጥገና ሥራ ፣ በኤሌክትሪክ ኃይልና በቴሌኮም የማስፋፊያ ሥራዎች  ወጣቱ በመደራጀት የራሱን ሥራ  ሊሠራ እንደሚችል አብራርተዋል ።
ያደጉ አገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፉ ለአገር  ኢኮኖሚያዊ ለውጥ   የማይናቅ  አስተዋጽኦ ሊያበረክት  እንደሚችል የገለጹት  ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቶች  ሥራነ ሳይንቁ ለአዲስ ሥራ  በመዘጋጀትና አመለካካት ችግሮቻቸውን በማስወገድ  ከራስ ለወጥ  ባሻገር ለአገር ዕድገት ገንቢ ሚና መጫወት ይችላሉ ብለዋል ።