ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቲዎዶሮ ኦቢያግን ንጉኤማ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙትን የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቲዎዶሮ ኦቢያግን ንጉኤማ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ፡፡

ሁለቱ መሪዎች ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ ጉዳዮችና በቀጣናዉ ሰላም ላይ ከመነጋገራቸው በተጨማሪ ዛሬ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀንን በማስመልከት በስደተኞች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ፕሬዝዳንት ንጉኤማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢኳቶሪያል ጊኒ ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈውላቸዋል።

በተጨማሪም በጽህፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞችን በጋራ መትከላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያና ኢኳቶሪያል ጊኒ ለዓመታት የዘለቀ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አላቸው።