ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ዜጎች ለጋራ ልማት እንዲነሱ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ታሪክ ይዘክረዋል

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕዝቦች  ለጋራ ልማት በአንድነት  እንዲነሱ ያደረጉት አስተዋጽኦ ታሪክ ሲዘክረው እንደሚኖር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።       

ምክር ቤቱ ለዋልታ በላከው መግለጫ እንደገለጸው የታላቁ  ህዳሴ ግድብ  ግንባታ  ዋና ሥራ አስኪያጅ  በመሆኑን  ሲያገለግሉ የቆዩት ኢንጂነር ስመኘው በህይወት ብናጣቸውም ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  በአንድነት  ለጋራ ልማት እንዲነሱ ያደረጉት  አስተዋጽኦ ትውልድና ታሪክ  ይዘክረዋል  ብሏል ።

በኢንጂነር ስመኘው በቀለ  ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት  የምክር ቤቱ  ሠራተኞች  ድንጋጤ  ቢሰማቸውም መላው የአገሪቱ ህዝቦችን በበለጠ ህዝባዊ አንድነትና የጋለ ወኔ በማስተባበር  ግድቡን  በማጠናቀቅ የቆምንለትን  ዓላማ እናሳካለን ብሏል በመግለጫው ።