የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት ሐምሌ 22 እደሚፈጸም ተገለጸ

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት እሁድ ሐምሌ 22/2010 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤቴክርስትያን እንደሚፈጸም ብሔራዊ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ገልጿል።

የቀብር ስነስርዓቱ ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት ለአንድ ታላቅ የልማት አርበኛ በሚደረግ ስነስርዓት እንደሚከናወንም ተመልክቷል።

የብሔራዊ ቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴው በእኝህ ታላቅ የልማት አርበኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቻው እና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ተመኝቷል፡፡ (የመንግስት ኮምዩንኬሽን ጽህፈት ቤት)