የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ተገለጸ

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከ8 ሰዓት ጀምሮ ይፋ እንደሚሆን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በመላው ሀገሪቱ በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፈተና 154 ሺህ 010 ወንዶች እና 127 ሺህ 964 ሴቶች በድምሩ 281,974 ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጿል።

ፈተናዎቹ ዓለም አቀፍ ተወዳሪነታቸው በተመሰከረላቸው ዘመናዊ አዳዲስ OMR (Optical Mark Reader) የማረሚያ ማሽኖችን በመጠቀም በጥራት የታረሙ መሆናቸውም ተነግሯል።

በመሆኑም ተማሪዎች ውጤቶቻቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ውስጥ የመፈተኛ ቁጥር በመጻፍ go የሚለውን አንዴ Click በማድረግ ማየት ይችላሉ ሲል ነው ያስታወቀው።