በጎ ፈቃደኞች በአዲስ አበባ መስጅዶችን አፀዱ

"አካባቢያችንና ዉስጣችንን እናፅዳ" በሚል መሪ ቃል በጎ ፈቃደኞች በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ መስጅዶችን የማፅዳት መርሀግብር አካሂደዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍል ከተማ በታለቁ አንዋር መስጅድ  በተካሄደዉ የፅዳት  መርሀግብር በርካታ ወጣቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

የክፍለ ከተማዉ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤፍሬም አድማሱ በክፍለ ከተማዉ የተለያዩ የበጎ ፈቃዲ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ለሀገራዊ አንድነት ጥቅም እንዳላቸዉ ተናግረዋል፡፡

የታላቁ አንዋር መስጅድ  አስተዳዳሪ ሀጂ  አበራ ቡስር  በፅዳት መርሀግብሩ ላይ “የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች ወንድሞቻችን መሳተፋቸዉ በተለያዩ ሀይማኖቶች መካከል ያለዉን አንድነትና መቻቻልን ያዳብራል" ብለዋል፡፡