የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተቸገሩ ተማሪዎችና ቤተሰቦች ድጋፍ እያደረገ ነው

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጎ አድራጎት ክበብ ለ50 ተማሪዎችንና 12 የሚሆኑ ለአካባቢዉ ቤተሰቦች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ በግቢዉ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከግቢዉ ዉስጥ አልፎ በአካባቢዉ የሚገኙና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች እየረዳሁ ነዉ ብሏል፡፡ ከገቢ ማስገኛ መንገዶቹ መካከል በግቢዉ ዉስጥ የሚካሄድ ካርኒቫል አንዱ ዘዴ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አሁን ደግሞ የቀድሞ የዩኒቨርሰቲዉ ተማሪዎች ባበረከቱት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አማካኝነት የበጎ አድራጎት ክበቡ ወደ ማዕከልነት ተሸጋግሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ አሁን ላይ  በተገኘዉ ዕርዳታ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተቸገሩ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተመስረተ 18 አመት ያስቆጠረና በኢትዮጵያ ቀደምት ከሆኑት የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ተጠቃሽ ነዉ፡፡