የሰላም ሚኒስቴር ከአለምአቀፍ የስደተኞች ኮሚሽን ጋር በስደተኞች አያያዝ ዙሪያ ተወያየ

የሰላም ሚኒስቴር ከአለምአቀፍ የስደተኞች ኮሚሽን ጋር በስደተኞች አያያዝ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ በትግራይ ክልል በአራት ካምፖች የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች አያያዝ ዙርያ ገለፃ ተደርጓል።

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ሙፈርሃት ካሚል ከ3ሺህ በላይ አዲስ ስደተኞች በካምፑ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸው፣ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒት እንዲሁም የውሃ አገልግሎት ተደራሽ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልል የሚገኙ አራቱ ካምፖች አለምአቀፍ ህግ የጠበቁ አለመሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከ26 አገራት የተወጣጡ ከ1 ሚለየን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ እንደምታስተዳድር የገለጹት ወ/ሮ መፈርሃት፣ ስደተኞች ሲስተናገዱ አለም አቀፍ ድንጋጌዎች ስተቀበልን ሳይሆን በእኛነት ስሜት ስደተኞችን ለመጠበቅ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

(በዙፋን አምባቸው)