የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ6 ወራት አፈፃፀም ከታቀደው 94 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል።
”ከ100 በላይ መሪ ቃላችን በማሳካት ለአዲስ አበባችን ብልፅግና የላቀ ገቢ እንሰበስባለን” በሚል የተዘጋጀ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የገቢ መጠን መቶና ከዚያ በላይ ማሳካት እንዲቻል ህግን በተከተለ መልኩ ገቢ የሚሰበስብ ከቴክኖሎጂ ጋር ቁርኝነት ያለው ታማኝ ሰራተኛ ለመፍጠር ግምገማና የአቅም ግንባታ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ገቢዎች ሞደርናይዜሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ውዴ ቴሶ ናቸው።
ሀላፊዋ አክለውም የ6 ወራት አፈፃፀም ስንገመግም ክፍተታችንን የምንሞላበት ጥንካሬያችንን የምናስቀጥልበት ይሁን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የግብር ቁጥጥር አላማዎች ከግብር ከፋይ የተለያዩ ስጋቶችን መሰረት በማድረግ መስራት፣ ለህግ ተገዚ ያልሆኑትን መከላከል እና ለህግ ተገዚ የሆኑትን ግብር ከፋዮች መደገፍ ተገቢ መሆኑ ተገልጿል።
በ6 ወራት ውስጥ የግብር ቁጥጥር (ኦዲት) 5.1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 5.3 ቢሊዮን መሰብሰብ ተችላል።
በአጠቃላይ ገቢ 24.281 ቢሊዮን ታቅዶ 22.88 ቢሊዮን ብር ገቢ ተደርጋል።
ይህም ከ2012 በጀ ዓመት ትጠቅላላ ገቢ ጋር ሲነፃፀር በ1.39 ቢሊዮን ወይም በ6 በመቶ እድገት ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።
አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና የግብር ከፋይ ማህበረሰብ አደረጃጀት አመራሮች በመጀመሪያ መንፈቅ አመት የዕቅድ አፈፃፀም ተገምግማል።
መድረኩ ለሶስት ቀናት እእንደሚቀጥልም ታውቋል።
(በሃኒ አበበ)