በሆለታ ልዩ ዞን ወልማራ ወረዳ ህዝቡን ያሳተፈ የተፋሰስ ልማት ስራ ተከናወነ

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልል ሆለታ ልዩ ዞን ወልማራ ወረዳ ህዝቡን በነቂስ ያሳተፈ የተፋሰስ ልማት ስራ ተከናወነ።

የወረዳ አርሶ አደሮች እና 25 የኦሮሚያ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመሆን የተፋሰስ ልማት በዛሬው እለት አከናውነዋል።

የአካባቢውን አርሶ አደሮች እና የመንግስት ሰራተኞችን ያሳተፈው የተፋሰስ ልማት መከናወኑ የአፈር መሸርሸርን እና የጎርፍ አደጋን ከመቀነስ አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተሳታፊዎች ለዋልታ ገልፀዋል።

የአካባቢውን አርሶ አደሮችም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአርሶ አደሩ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የተፋሰስ ልማት ስራውን በተጠናከረ መልኩ መስራት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራውን እንደሚያሻሽለውም ተናግረዋል።

(በደረሰ አማረ)