በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከጥር 14 እስከ 20፣ 2013 ዓ.ም ድረስ 64,025,470.75 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ሀገር ለማስገባት እና ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋ 48,382,510.75 ብር ሲሆን፣ 17,642,960 ብር የሚገመት የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ ኬላዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል መድኃኒት፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የትምባሆ ውጤቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡
የሚኒስቴሩ መረጃ እንደሚያመለክተው ዕቃዎቹ በጉምሩክ ሰራተኞች እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በህብረተሰቡ ርብርብ የተያዙ ናቸው።