341 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

76 ህፃናትን ጨምሮ 341 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ።

በትላንትና ዕለት ወደ አገር የተመለሱትን ዜጎች ከህፃናት ውጭ 265 ሴቶች ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።