ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ለሚገነባው የኢሰ ቦሩ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከሚያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች አካል የሆነው ትምህርት ቤቱ የሚገነባው የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን የትውልድ ስፍራ በሆነችው ቦሩ ጎረምቲ ቀበሌ ነው።
ትምህርት ቤቱ በሚገነባበት አካባቢ 10 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የተነሳ የአካባቢው ተማሪዎች ረጅም ርቀት ተጉዘው ለመማር ይገደዱ እንደነበር ተገልጿል።
16 ክፍሎች የሚኖሩት ትምህርት ቤቱ በውስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የቤተ መጽሐፍት፣ የኮምፕዩተር፣ ላብራቶሪ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች እንምኖራቸውም ተጠቁሟል።
የትምህርት ቤቱ የመሰረተ ድንጋይ ማኖር መርሃግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከቀዳሚዊት እመቤት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።