የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአንካራ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረቁ

የካቲት 08/2013 (ዋልታ) በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት ተመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ ተገኝተዋል።

ኤምባሲው በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መሰረተ ድንጋዩ ተቀምጦ ባለፉት አራት ዓመታት በግምባታ ላይ ነበረ።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቩሉት ካቩሶግሉ አዲሱ ኤምባሲ መገንባቱ የኢትዮጵያ እና የቱርክን ግንኙት እንደሚያጠናክር መግለፃቸው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።