ዶ/ር ሂሩት ካሳው 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለማክበር አሶሳ ከተማ ገቡ

 

125ኛው የአድዋ ድል በዓል

የካቲት 17፣ 2013 (ዋልታ) 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማክበር የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው አሶሳ ከተማ ገቡ።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራርም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በዓሉም ከዛሬ ጀምሮ በፓናል ውይይት እና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡