የካቲት 18/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ ከክልል ፕሬዚዳንቶች እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ጋር መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
በበይነ መረብ በተካሄደው በዚህ ውይይት በመጪው ምርጫ ዙሪያ ትኩረት ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡
በውይይቱም ክልሎች በመጪው ምርጫ ጸጥታና ሰላምን ከማስከበር፣ እንዲሁም አስፈላጊውን ግብዓት ከማሟላት አኳያ ያላቸውን ዝግጅት መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በትናንትናው ዕለትም ከፌደራል እና ከክልል አመራሮች ጋር በምርጫ ዙሪያ መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎች መቀመጣቸውም ነው የተጠቀሰው፡፡