የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የካቲት 19/ 2013 (ዋልታ) – የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከበጀቱ ለትግራይ ክልል የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ ተጨማሪ ሃብት የማሰባሰብ ስራ መጀመሩንም ገልጿል፡፡

አስተዳደሩ በቀጣይ ተጨማሪ ሃብት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማሰባሰብ የሚያስችል ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን አመልክቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው በትግራይ ክልል በተከናወነው የህግ የማስከበር ዘመቻ የጁንታው ሐይል ያደረሰውን ውድመት ተከትሎ በአካባቢው የከፋ የሰብአዊ ጉዳት በመድረሱ እንደሆነ በፌስቡክ ገጹ ማስነበቡን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡