ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ125ው የአድዋ ድል ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የካቲት 22/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች ለ125ው የአድዋ ድል ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያዊነት ልዕልና፣ የትናንት ደማቅ ታሪክ፣ የዛሬ ትውልድ ወኔ እና የነገ ተተኪዎች ስንቅ ለሆነው 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲሉም ነው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

125ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ ከንጋቱ 11 ሰዓት 30 ጀምሮ በመዲናዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ያስታወቁት ምክትል ከንቲባዋ፣ ከንጋት ጀምሮ ከአራቱም የከተማዋ አቅጣጫዎች ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር የድል በዓሉን ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል፡፡

የአድዋ ዘማቾች መሰባሰቢያና መነሻ በሆነችው አዲስ አበባ፤ ከባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነው የአድዋ ድል በዓል  በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበርም ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል፡፡