በምስራቅ አፍሪካ ውስን አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል- ኢጋድ

መጋቢት 07/2013 (ዋልታ) – በምስራቅ አፍሪካ ውስን አካባቢዎች እጅግ ከፍተኛና ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስታወቀ።

ኢጋድ በየሳምንቱ በሚያወጣው የቀጣናው የአየር ትንበያ ሪፖርቱ እንዳስታወቀው፣ በሳምንቱ በማዕከላዊ ኬንያና ደቡባዊ ታንዛኒያ እጅግ ከፍተኛና ከፍተኛ ዝናብ ይጠበቃል።

በቡሩንዲ፣ ምዕራብ ርዋንዳ እና በምዕራብ ታንዛኒያ የተወሰነ ክፍል መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ደቡባዊ ሶማሊያ፣ ምስራቅና ምዕራብ ኬንያ፣ ሰሜናዊ ታንዛኒያ፣ ምዕራብ ዩጋንዳ እንዲሁም ደቡብ ሱዳንና ደቡባዊ ኢትዮጵያ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

አብዛኛው ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሰሜናዊና ደቡብ ምስራቃዊ ኢትዮጵያ፣ ሰሜናዊ ሶማሊያ፣ ሰሜን ምዕራባዊ ኬንያ እና ምስራቃዊ ዩጋንዳ ደረቃማ ሆነው ይቆያሉ።