በምስራቅ ጎጃም በመጪው ክረምት የሚተከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ተዘጋጀ

መጋቢት 23/2013 (ዋልታ) – በምስራቅ ጎጃም ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአርሶ አደሩ ዘንድ እየተለመደ የመጣውን የቡና ልማት ለማስፋፋት በመጭው ክረምት የሚተከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የመስኖ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ አህመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አርሶ አደሩ ከሰብል በተጓዳኝ ቡና በማልማት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተጀመረው የቡና ልማት 1 ሺህ 500 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ 1 ሺህ 170 ሄክታር ማሳ መሸፈኑን ተናግረዋል።

የተገኘውን ልምድ በማስፋት በመጪው ክረምት የሚተከል 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የቡና ችግኙ 350 ሄክታር አዲስ መሬት ላይ የሚተከል መሆኑን አመላክተዋል።

የተዘጋጁት የቡና ችግኞች በሽታ ተቋቁመው በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ምርት መስጠት