ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

ዶ/ር አብርሃም በላይ
ሚያዚያ 28/2013 (ዋልታ) – ዶክተር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አብርሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ።
ዶ/ር አብርሃም ከእነዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል።
ከእነዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የድሮ ሜቴክ፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ የአምቦ ዩንቨርሲቲን በቦርድ ሰብሳቢነት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ አባል በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ።